Life Story

የወ/ሮ ምርጥዓለም ታከለ አጭር የሕይወት ታሪክ

ወ/ሮ ምርጥዓለም ታከለ ከአባቷ ከአቶ ታከለ ዉቤና ከእናቷ ከወ/ሮ አዳነች ገዳ በ1956 ዓ.ም በአዋሳ ከተማ ተወለደች።በታህሣሥ አቦ የፈነጠቀችው ጮራ ገና ከህጻንነቷ ጀምሮ በላይዋ ላይ የፈሰሰው ፀጋ ትንሽ ትልቁን ማራኪ ሆና ነበረ የተፈጠረችው።የምርጥዓለምን ታሪክ ከመቀጠል በፊት የክርስትናና የዓለም ስሞቿን አመጣጥ መግለጽ ምንነቷን በጥቂቱ አቅጣጫ ያሳየናል፡ እንዳሰው።

በኦርቶዶክሣዊ እምነት የክርስትና ቀኗ አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ የክርስትና እናቷ ወ/ሮ የሺ እንደሚሆኑ የታወቀ ነበረ፡ ነገር ግን መጨረሻው ሠዓት ሲቃረብ ወ/ሮ የሺ ክርስትና አላነሳም አሉ፡ ምክንያቱን ሲገለጹ ከርስዋ በፊት ክርስትና ያነሷት ታላቅ እህቷ ስለሞተች ሐዘን ጎድቶኛል፡ ይህቺም ከሞተች ሃዘኑን አልችልም በማለት ነበረ ስጋታቸውን የገለጹት፡ ቤተሰቡም ምርጥዓለምን ለታቦት ለመስጠት ወስነው ሲያድሩ እንደገና ወ/ሮ የሺ በለሊት ሰው ከመነሳቱና ወደቤተከርስቲያን ከመሄዱ በፊት ሃሳባቸውን መቀየራቸውንና ልጅቱን ክርስትና ለማንሳት መወሰናቸውን ሲያበስሩ በእንዲህ አይነት መልክ ነበረ። ሌሊት በህልሜ  አንድ አዛውንት ሰው መጥተው የሺ ይህቺን ብላቴና ክርስትና አንሺ፤ ስሟንም ሚሥጢረ ሥላሴ በያት ባሉት መስረት ወ/ሮ የሺም ክርስትናውን አነሱ።   ምርጥዓለምም የሚሥጢረ ሥላሴን ስምን ይዛ እነሆ እስከ ዛሬ ቆየች።

ምርጥዓለም ታከለ  የመጀመሪያዋን ዓመት በሰናይት ታከለ ትጠራ ነበረ፡ ድንገት አንድ ጥዋት እንደ ክርስትና እናቷ አባቷ አቶ ታከለ ውቤ ከመኝታ ተነስቶ በወቅቱ የነበሩ እናቱንና ሌሎቹንም በማስነሳት ከዛሬ ጀምሮ ሥም ሊቀየር ነው፡ ዛሬ ሌሊት በህልሜ አሉ አቶ ታከለ ልክ እንደ ወ/ሮ የሺ፡ ለሊት በህልሜ  አንድ አዛውንት ሰው መጥተው ይህቺ ብላቴና ማን ነው ስሟ? ብለው ጠየቁኝ፡ እኔም ሠናይት ትባላለች ስላቸው የለም ይህቺማ ምርጥዓለም ነች ብለውኛል በማለት ከዚያን ዕለት ጀምሮ ምርጥዓለም፤ ምርጥዓለም ተብላ መጠራት ጀመረች።

የእድገቷ መነሻ የነፍስ ማወቂያዋ አድራሻ በጎላ ሚካኤልና በአንበጣ መከላከያ ነበረ፡ በስፈሩ ባሉ የኔታ የመጀመሪያውን ፊደል እዛው ፖሊስ ሰፈር ባለው በክቡር ራስ መስፍን ስለሺ ት/ቤት በአሁኑ አጠራር የኢትዮጵያ እርምጃ ከ1ኛ እስከ 8ኛ አጠናቃለች።  ምርጥ፤ ከዲያረክትሮች እስከ መምህራኖቹ፤ ከጽዳት እስከ ጥበቃ ሠራተኞች ባጠቃላይ በተማሪዎች ዘንድ ምርጥዓለም ታከለ እንደ ጨረቃና ፀሃይ ገፋ ሲለም በመንፈሳዊ ዓለም  እነደሚያበሩ ከዋክብቶቸ እንደ አንዷ ተደርጋ የምትታየው በውጫዊ ውበቷ ብቻ ሳይሆን ከበረዶ የነጻ ውስጥዋ ደግነትዋን ስለሚመሰከርላት ነው።

ምርጥዓለም የጣፋጭና የኮልታፋ አንደበቷ አፍ መፍቺያ ቃል የእምነቷ ቁልፍ የሆነችው ኪዳነምህረት፤ ጽናቷ በኪዳነምህረት፤ ፍቅሯም ሁሉም ነገር ኪዳነምህረት።  ይህ ነው በቅርብ ሰዎቿ መለያ መታወቂያዋ ምልክቷ። ምርጥዓለም የቤቷ ኮከብ፤ የትዳሯ እመቤት፤ ሠፈሩ አገሩ ሁሉም ያፈቅራታል፡ ሚስጢሩ ግን ምንድነው ከተባለ ሁሉንም የሰው ልጅ እኩል ስለምታፈቅር ነው።

ምርጥዓለም የሁለንተኛ ደረጃ ትምህርቷን በባልትና ሳይንስ ከጄነራል ዊንጌት ተመርቃ ቤተሰቦቿን ለመርዳት የተለያዩ ስራዎችን ብትሞክርም ነገር ግን በዋናነት አፍቃሪ አባቷ አቶ ታከለ ውቤ በወጣትነት በሞት ስለተለያት ሃላፊነቷን ለመወጣት በተለይ እናቷ ወ/ሮ አዳነች ገዳ ዛሬ በሕይወት ኖረው የምርጥን መለየት እንደ እንቆቆ የተጋቱትን ለማሳረፍ ስትል የቤቱንና የማዕድቤቱን ስራ ተረክባ ቤተሰቡን ቁጭ አድርጋ ሃላፊነቷን ተወጥታ ነበር፡ የመጀመሪያና የመጨረሻ ውድ ባለቤትዋን አቶ መኮንን በጋሻውን ለመቀላቀል ወደ አሜሪካ ሎስአንጀለስ እስክትመጣ ድረስ ማለት ነው።

ትንሽ ደግሞ ስለ ባህርዮቿ እንጥቀስ፡

*  በሳቋ ድፍን አገር ያውቃታል፡ ያውም ሕይወት የተላበሰ የውስጥ ፈገግታ!

*  ምርጥዓለም ተጫዋ፤ ቀልደኛ፤ አስቂኝ ፍጡር እንደነበረች እድሉ የገጠማቸው ያውቃሉ፡

*  ምርጥ ሀዘንተኛን ለማፅናናት፤ ላስተዛዝነው ሳይሆን ላድምቅለት ብላ ነበር የምትነሳው፡

*  ምርጥዓለም ለሁሉ ሰው ትጨነቃለች፡ ጭንቀቷ ከከንፈር መጠጣ የዘለለ መሆኑን የተጨነቀችላችሁ፤ የተጨነቀችልን ሁላችንም ስለምናውቀው  ላላወቁት ለማስረዳት ይከብዳል።

ከሃያ አምስት አመት በፊት ወደ አሜሪካ ሎስአንጀለስ መጥታ ፍቅርን ሰጥታ፤ ፍቅርን ተቀብላ ሁለት መሰሎቿን ሜሮን መኮንንና ሜላት መኮንንን አፍርታለች፡ ልጆቿን ወለደች ቢባልም በአምሳሏ በሃይማኖትና በሥነምግባር በኢትዮጵያዊነት አንጻለች ቢባል ተገቢ ቋንቋ ነው፡ ምርጥ ልጆቿን በማሳደጉ ቡዙ ጊዜ አሳልፋ መስራት ባስፈለጋት ጊዜ ስራ የገባችው ሕጻናትን ማስተማር ነበር፡

በተፈጥሮ ያላትን የእግዜር ሥጦታ ከዘመናዊ ትምህርት ጋር በማዛመድ የህጻናት አስተዳደግ ትምህርትን ተከታትላ በዲፕሎማ ተመርቃለች፡ በዚሁ ሙያዋ ለረጅም ዓመታት ስትሰራ እያለች ነው ከአንድ ዓመት በፊት አስደንጋጭ ሕመም ያገኛት፡ ይህን ለስም የከበደ ብዙዎችን የተፈታተነ በሽታ ምርጥዓለምን አላስደነገጣትም፤ ተስፋም አላስቆረጣትም፤ እምነቷን አለተፈታተናትም፤ ፍቅር አልነሳትም፤ የተፈጥሮ ሳቋን አልገፈፋትም፡ ምርጥ ይህን ዲያቢሎስ አሽንፋው እንዳመነች እግዚአብሔርና ፍቅሯ ያፈራላት እንደ አሽዋ ያበረከተላትን ጓደኞቿ፤ ባለቤቷ፤ ልጆቷ፤ እህቶቷ፤ ወንድም ቤተዘመዶች፤እየተንከባከቧት ያለ እድሜዋ ግን ጌታ በቆረጠላት ጊዜ በቤተሰቦቿ  እጅ በጓደኞቿ እቅፍ በምትወዳት በእናቷ ኪዳነምህረት ቀን በወላጅ እናቷ የልደት ቀን በደመራ በመስቀሉ ዋዜማ እለት አርብ ከዚህ ዓለም በድል ተስናብታለች።

አንዳንድ ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች፡

*  ወሎ ክ/ሐገር ግሽን ማርያም አካባቢ የሚገኝውን ደንቆት መድሐኒዓለምን የጎጆ ሳር ቤት በዘመናዊ ቆሮቅሮ በማስራት

*  በአደራ የተቀበለችውን በግሸን ማርያም የሚኖሩ አረጋውያን አባቶችን በመርዳት

*  አዲስ አበባ ግቢ ገብራኤል ውስጥ በምትገኝው ባህታ ማርያም አቅመ ደካሞችን ለመርዳት በአባልነት ተመዝባ በእለተ ደብረ ታቦር አመታዊ እርዳታዋን ታካሂድ ነበር

*  ጎሽ ባዶ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን ሽዋ ክ/ሐገር ተጉለት ውስጥ በማደስና አልባሳት በማቅረብ

*  በደብረሊባኖስ ገዳም የደካሞች ማረፊያ ቤት በማሰራት ያደረገችው አስተዋጸዎና አስተባባሪነት ከቡዙዎቹ ገድሎች በጥቂቱ ነው።

*  እዚሁ ሎስ አንጅለስ ደግሞ በድንግል ማርያም ኦርቶዶከስ ቤተ ክርስቲያን በሕዝብ ግንኙነትና በሕጻናት ትምህርት ኮሚቴ ውስጥ በመሳተፍ አገልግሎት አበርክታለች፡ እንዲሁም በመድሐኒአለም እህትማማቾች  ማህበርና በኪዳነምህረት እህትማማቾች ማህበር ውስጥ በአባልነትና በአመራር ስራ በማገልገል ማህበራዊና መንፈሳዊ ግዳጇን ተወጥታለች።

  4 comments for “Life Story

 1. Emebet
  November 5, 2014 at 9:36 am

  I can’t believe my beautiful cousin gone so early.
  Dear Mekonnen, Melat and Meron, While nothing that I can say will make you feel better at this time, I would like you to know that I am always here if you need anything.
  R.I,P Kukusha, with lots of love
  Emebet

 2. November 18, 2014 at 8:54 pm

  “Yena Konjo”

  I wish I could express it
  In my own tongue

  Not I chose to write it
  In different language
  Simply I don’t have the software

  However, no matter in what idiom
  It is written; it has the same definition

  “Yena Konjo” means my beauty
  You remaining the same
  Always everyone’s “Konjo”

  Thus, unforgettable past
  All the remembrance is unwavering

  Beauty or kindness is not valued to earth
  But very much to us

  Family and friends, I know what you would be feeling
  During this Holiday Season

  May the Lord give you the strength
  To continue your journey

 3. October 20, 2017 at 2:48 am

  The Cloud
  The foam of clouds spreads high above
  Like farm of cottons in the field
  Looks as it is a winner

  The air broke out of breath
  The sun playing hide and seek
  From birds nibbling dry grass

  To garden flowers, lake and river
  The falling leaves from dryness
  And all watching up for its rapture

  A day deep and long
  Earth is dry and tolerance with little to do
  The dryness hurting all

 4. October 20, 2017 at 2:52 am

  R o s e s
  As a garden full of roses
  Over flowing the smell
  The delightful look with beautiful colors

  For mind challenging to decide
  Which colors best to pick
  Red, yellow, pink or purple

  No rain, snow and wind to ruin
  All the frosts over gone
  In blossoms after blossoms
  What a joyful look?

  Oh, how to appreciate and admire the nature
  That is one way of joy to be around
  The garden of Roses

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *