Her Husband’s (Mekonnen Begashaw) Poem

ምርጥዬ ኩኩሽዬ አለምዬ

ውዴ ነበርሽ ጓደኛዬ አማካሪዬ

እህቴም ነበርሽ ተቆርቋርዬ

እናቴም ነበርሽ አሳቢዬ

ባለቤቴም ነበርሽ ግማሽ አከላቴ

የልጆቼ እናት ቤቴ መሠረቴ።

ትዳራችን ሞቆ ሞገስ አልብሰሺው

በፍቅር ነጸብራቅ ሕይወትን ሰጥተሺው

ደስ ብሎን ስንኖር ልጆች ስናሳድግ

የሰው ኩራት ነበርን የትዳር ማእረግ

top essay writer get link erexin spray reviews https://raseproject.org/treat/levitra-loveland/97/ accounting research paper help latex homework art therapy thesis essay synonym changer go to link source url christian ethics abortion essay go to link verbe essayer futur simple follow link answer essay gre question real fast shipment viagra source url watch tips for writing thesis conclusion https://carlgans.org/report/past-exam-papers-for-igcse/7/ see can take viagra tylenol get help with homework viagra releases personal statement examples for university homeowrk help what do you put on a cover letter viagra online prices https://raseproject.org/treat/levitra-le-claire/97/ homework service homework helpers u s history health services research and policy ኩኩሻዬ

ማዕረጌ ነበርሽ ጉልላቴ

የእኔነቴ መመኪያ ኩራቴ

ውዴ ነበርሽ ፍቅረኛዬ

የልጅነት  ጓደኛዬ

የልጆቼ እናት ሕይወቴ

የመጀመሪያዋ የትዳር መሠረቴ

በንጽህና ያገኘሁሽ እህቴ

ቸኮልሽብኝ ለመለየት አከላቴ

ምርጥዬ

የትዳሬ ውበት፣ የቤቴ ምሰሶ

ፍቅርን ከውበት ጋር የሰጠሽ አላብሶ

አንደበትሽ መልካም፣ ክፉ የማይወጣው

ሃሰት የሌለበት፣ በእውነት የተሞላው

ትልቁም ትንሹም እኩል ነው በፊትሽ

አድልኦን የማታውቂ እግዚኣብሔር ሲፈጥርሽ

ማስቀየም አታውቂ ከማስደሰት በቀር

በትህትና ያጌጥሽ በፈጣሪሽ ፍቅር

ኩኩሻዬ

ሁል ጊዜ ተጫዋች፣ ሁል ጊዜ ፈገግታ

የደስታዬ ምንጭ፣ የሕይወቴ አለኝታ

ሳዝን አጽናኛዬ ሲከፋኝ መካሪ

አጣሁሽ እህቴ የኔ ተቆርቋሪ

የእውነት ተለየሺኝ? ጨክነሽ?

እኔስ ልቅር፣ ግን ልጆችሽን ለማን ጥለሽ?

የሩቅ መንገደኛ ከሄዱበት ላትመለሽ፣

ከአድዬ ከናትሽ ጨክነሽ ተለየሽ?

ኩኩሻዬ

የድሃ እናት ነበርሽ፣ ላጣ ሰው አሳቢ

ኑሮ ላሸነፈው ለጠፋው ሰብሳቢ

ይናገሩ ጓደኞችሽ በረንዳ አዳሪዎቹ

አቅም ያነሳቸው ሚስኪኖቹ

ይመሰክራሉ ደግነትሽን

ያደረግሺውን ትሩፋትሺን

ምርጥዬ

አምላክ ግን ለወጠው ሁሉንም ለበጎ

ማለፍሽ እንዲሆን ምክንያቱን ፈልጎ

ተመሰገነበት ኢየሱስ ክርስቶስ

የዓለም ፈጣሪ የንጉሶች ንጉሥ

በአንቺ ማለፍ ምክንያት ጌታችን ከበረ

ወንጌል ተሰበከ መዝሙር ተዘመረ

ሐዘኑን ለወጠው በዝማሬ ጌታ

ተመሰገነበት ከጠዋት እስከ ማታ

ማጽናናት ታውቃለህ ክርስቶስ ጌታችን

በዘመድ አዝማዱ በወዳጅቻችን

በፍቅርህ አስዋብከን ቆመህ ከጎናችን

አበስክልን አምላክ እንባን ከአይናችን

ኪድዬ

እመቤቴ ማርያም ኪዳነምህረት

ድንቅ ነሽ በእውነቱ የምርጥዬ እናት

ኪድዬ ወዳጅሽ ሁሌ ካንቺ ጋራ

እምታነጋግርሽ እንደ ባልንጀራ

አንስታሽ አትጠግብም፣ ስምሽን ስትጠራ

ኪድዬና ምርጤ ፍቅራችሁ ልዩ ነው

ሚስጢራችሁ ቡዙ ማንም የማያውቀው

በቀንሽ ጠራሻት ልጅሽን  ሰበሰብሻት

በቅፍሽ ለማኖር በቀኝ ልታቆሚያት

ምርጥዬ

ፍቅር ሰላማዊት ትህትና ፈገግታ

ልዩ ምልክትሽ የእግዚኣብሔር ስጦታ

በልቤ ላኖረው ቃል ገባሁ ከፊትሽ

የኔም ጊዜው ድረሶ እስከምከተልሽ

ይኑር በሕይወቴ ልዩ ምልክትሽ

ኩኩሻዬ

አምላክ መረጠሽ ወደደሽ

የራሱ ምርጥ እቃ አረገሽ

እስከማይሽ እስካገኝሽ

ደህና ሁኚ አከላቴ ልሰናበትሽ

ፍቅሬ እወድሻለሁ

ከውድ ባለቤቷ መኮንን በጋሻው

  1 comment for “Her Husband’s (Mekonnen Begashaw) Poem

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *